በስም የከበረ..
አንድ እስክንድር የተባለ
ንጉስ ሃይለኛ ውጊያ ነበረበት፡፡ ወደ ጦር ሜዳወው ሔዶ የወታደሮቹን ውሏቸውን እየጎበኘ ሳለ ከርቀት አንድ የሚሮጥ ወታደር ያያል፡፡ሩጫው
ያሽሽት ስለነበረ የጠላት ይሁን የሱ ወታደር ከርቀቱ የተነሳ መለየት ስላልተቻለ አጠገቡ ያሉትን ወታደሮች ይዘው እንዲያመጡለት አዘዛቸውና
ይዘውት መጡ፡፡ ንጉሱ ወታደሩን አስተውሎ ተመለከተውና ‹‹ከጠላቶቻችን ወገን ነህ ? ውይስ ከኛ ወገን ነህ ወዳጄ?››ብሎ ጠየቀው
ወታደሩም ‹‹ኸረ የእርስዎ ወታደር ነኝ ነረጉስ ሆይ!›› አለ በፍርሃት ‹‹ለመሆኑ ስምህ ማን ነው ›› ሲሉ ጠየቁ ንጉሱ ወታደሩም
ቆፍጠን ብሎ ‹‹ እስክንድር እባላለሁ ወታደር እስክንድር ›› አለና መለሰ፡፡ ንጉሱ እንደማዘን እንደመተከዝም አሉና ‹‹እስክንድር!
ወይ እንደኔ ተዋጋ አልያም ስሜን መልስ›› አሉት ይባላል፡፡ ድንቅ አባባል ነበረ፡፡
ወገኖቼ ዛሬም ስንት
ሰው አለ መሰላችሁ ስሙ ክርስቲያን ሁኖ ግብሩ የአህዛብ የሆነ ፡፡ከስራችን በፊት ስማችን መቅደም የለበትም፡፡ ስራችን ስማችንን
ይግለፅ እንጂ በስማችን ብቻ ልንጀነን አይገባም ክርስቲያኖች ነን? ከሆንን ደግሞ እንደ ቀደሙት ክርስቲያኖች ልንኖር ያስፈልጋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ