…..ሰው ባያይ ……
ሁለት ሰዎች ይካሰሱና ከአንድ ሹም ይደርሳሉ፡፡ ጠቡ የተፈጠረው አንዱ ገንዘብ
አበድሬዋለሁ ይክፈለኝ ሲል ሌላው አልተበደርኩም አልከፍልም በማለቱ ነው፡፡ ሹሙ አበዳሪውን ሲጠይቁት ‹‹ይህ ባልነጀራዬ ወደ ቤተ መጣና ችግሩን አወያየኝ እኔም ባለቤቴ
እንዳጣይ ወደጓሮ ወስጄ አንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ተቀምጠን እኔና እሱ ብቻ ሆነን አንድ ሁለት ብዬ ቆጥሬ ሰጥቼዋለሁ ›› አላ፡፡
ተበዳሪው ሲጠየቅ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ በመማል ‹‹አለየሁም›› አለ፡፡ ሹሙ የሁለቱንም ሰምተው ሲያበቁ ተበዳሪውን
ጠርተው በሁለታችሁ መሃል የሚመሰክር ሰው ባለመኖሩ የሁለታችሁን ነገር ማወቅ ቸገረ ሰለዚህ ‹‹በል አሁን ሂድና እጓሮ አለ የተባለውን ትልቅ ድንጋይ ተሸክመህ
አምጣው እሱ እንዲመሰክር እናደርጋለን›› አሉ፡፡ ይሄኔ ተበዳሪው ቀበል አድርጎ ‹‹እንዴ ጌታው! ድንጋዩ እኮ ትልቅ ነው ለብቻዬ
አይሆንልኝም ›› አለ፡፡ ሹሙም አጭበርባሪነቱን ተረድተው ‹‹ብሩን ካልተበደርክ እሰውዬው ጓሮ ያለውን ድንጋይ ምን ስታደርግ አየኸው!
›› ብለው ተገቢውን ፍርድ ፈፅመው አሰናበቷቸው ይባላል፡፡
በሰው ዘንድ አልታይም
ብለን የምንፈፅማቸውን በደሎች ሳነስበው በራሳችን አጋላጭነት እግዚአብሔር ሊከስተው ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰው አለየም ዐላወቀም ብለን
ከመዘናገት ይልቅ በሰራነው ሃጥያት ተፀፅተን ንስሃ እንግባ፡፡ለወደፊቱም ይህን ከመሰለ ሸፍጥ እንራቅ፡፡ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሄርን
እንፍራ ሰው ባያይ እግዚአብሔር ያያል ዘፍ፡-"9.9 ‹‹እግዚአብሔር የተጣለውን ላምባ ነጋዴ ሌሊቱን ቀን ያደርግበታል፡፡››
ይባላልና፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ