ህግ እና ደንብ

አንቀጽ 1
የሰ/ት/ቤቱ ስያሜ እና ባሕሪ
1.1    የሰ/ት/ቤቱ ስያሜና ባህሪ በአጠቃላይ ሰ/ት/ቤት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህ ደንብ ባለበት ሀገርና አጥቢያ ቤተክርስቲያን ስም የአንፎ አዲስ ሰፈር መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አንቀፀ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት እየተባለ ይጠራል፡፡ የተቋቋመበት አላማ በቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ ዓዋዲ) መሠረት ሲሆን ወጣቶችን እና ሕፃናትን በክርስቲያናዊ ህይወት ለማነጽ ነው፡፡
አንቀጽ 2 
ራዕይ እና ተልዕኮ
2.1ራዕይ፡- በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ሕፃናት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እምነት እና ሥርዓት የሚሄዱ ሆነው በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እንዲሁም በክህነታቸው ሲያገለግሉ እና በዓላማዊው በአስኳላው ትምህርታቸው ውጤታማ ሆነው ማየት፣
2.2     ተልዕኮ፡-

2.2.1         በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ሕፃናትን ትክክለኛውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ትምህርተ ሃይማኖት እና የአብነት ትምህርት በማስተማር የቤተክርስቲያኗን ዶግማ፣ሥርዓት፣ትውፊት፣ታሪክ እና ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያውቁ ማድረግ፣
2.2.2       የተለያዩ እምነት መሰል ድርጅቶች በሚያደርጉት አባላት እንቅስቃሴ እንዳይነጠቁ አስፈላጊውን ሁሉ እንቅስቃሴ ማድረግ፣
2.2.3       የተለያዩ መንፈሳዊ ጉባዔዎችን እና ጉዞዎችን በማጋጀት ለምዕመኑ ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር፣
2.2.4       ለአባላት እና ለአጥቢያው ምዕመናን የበጎ አድራጐት ሥራዎችን መስራት እና የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፡፡

                                        አንቀጽ 3
አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
3.1 የኢትዮጵያ፣ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ የሆነ/ች/
3.2 በሰ/ት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ ለመመራት ፈቃደኛ የሆነ/ች/
3.3 ዕድሜው/ዋ/ ከ 4 ዓመት በላይ የሆነ
3.4 በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጠውን የቀዳማይ ተከታታይ ትምህርት ወስዶ/ዳ/ ፎርም የሞላ/ች/
3.5 በግቢጉባኤ፣በሰ/ት/ቤት እና በተለያዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲያገለግል ቆይታ/ቶ ማስረጃ ይዞ/ዛ ከመጣ/ች ለ3 ወር እንቅስቃሴው/ዋ ታይቶ በሥራ አስፈፃሚ ሲወሰን፣
3.6 በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጠውን ቀዳማይ ኮርስ በሥራ፣በትምህርት እና በመሳሰሉት አሳማኝ ምክንያቶች መውሰድ የማይችሉ ከሆነ ለ6 ወር በሰ/ት/ቤቱ ሳምንታዊ መርሐ ግብራት እንቅስቃሴው ታይቶ በሥራ አስፈፃሚ ከተወሰነላቸው፣
7.7 በአጥቢያው ያሉ ካህናት እና ዲያቆናት አባል ለመሆን በፈለጉ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ከአጥቢያው ውጭ የሆኑ ካህናት እና ዲያቆናት ግን ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
3.8 ከሌላ እምነት የመጣ/ች/ ሆና/ኖ በአጥቢያ ቤተክርስትያን በቃለ ዓዋዲው መሰረት ተምሮ የተጠመቀ ከሆነ እና አባል ለመሆን የሚያስችሉ መሰፈርቶችን ካሟላ/ች አባል መሆን ይችላል/ትችላለች፡፡
     3.9 አዲስ አማኝ ሆኖ ከሌላ አጥቢያ መረጃ ይዞ የሚመጣ ከሆነ በሰ/ት/ቤቱ 3 ዓመታት 
           ቆይቶ ለአባልነት የሚያበቁ መስፈርቶችን ካሟላ በኋላ አባል መሆን ይችላል፡፡







አንቀጽ 4
የአባላት መብት እና ግዴታ

4.1 የአባላት መብት
4.1.1 ማንኛውም አባል በጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ እና እንደደረጃው መርሐ ግብሮች ላይ የመገኘት መብት አለው፣
4.1.2 ማንኛውም አባል መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጡ  አገልገሎቶችን የማግኘት መብት አለው፡፡
            ማለትም    – የማጠናከሪያ ትምህርት እና የመሳሰሉትን
4.1.3 በ አሳማኝ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ሲዘዋወር መሸኛ የማግኘት መብት አለው፣
4.1.4 በደስታ እና በሀዘን ጊዜ ሰ/ት/ቤቱ በሚያወጣው መስፈርት መሰረት ድጋፍ  የማግኘት መብት አለው፣
4.1.5 አንድ አባል በፈቃደኝነት አባል መሆን አልፈልግም ብሎ በጽሑፍ ካቀረበ  ተቀባይነት ይኖረዋል፣ ነገር ግን መሸኛ ወረቀት አይሰጠውም፡፡
4.1.6 ማንኛውም አባል ሰ/ት/ቤቱ የሚያወጣውን መስፈርት ካሟላ በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጡ ስልጠናዎች እና ሌሎች አገልግሎቶች የማግኘት መብት አለው፡፡
4.1.7 ማንኛውም አባለ ለሰ/ት/ቤቱ በጽሑፍ እና በቃል ሐሳብ የመስጠት መበት አለው፣
4.1.8 ሰ/ት/ቤቱ የሚያወጣውን መስፈርት ካሟላ በሥራ አስፈፃሚነት የመመረጥ እና የመምረጥ መብት አለው፣





4.2 የአባላት ግዴታ

4.2.1 የሰ/ት/ቤቱ አባላት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ፣ትውፊት እና ሥርዓት መጠበቅ እና በእርሱ የመመራት ፣
4.2.2 በሰ/ት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ የመመራት፣
4.2.3 ወጣቶች እና ጎልማሶች በሰ/ት/ቤቱ ሳምንታዊ (እሁድ) መርሐ ግብር እና የጸሎት መርሐ ግብር (ረቡዕ) ላይ የመሳተፍ ፣
4.2.4 ሕፃናት በሰ/ት/ቤቱ የሕፃናት ሳምንታዊ (ቅዳሜ) መርሐ ግብር እና የጸሎት መርሐ ግብር (ረቡዕ) ላይ የመሳተፍ ፣  
4.2.5 የንስሃ አባት የመያዝ ፣
4.2.6 ወርሃዊ አስተዋጽኦ የመክፈል፣
4.2.7 ሰ/ት/ቤቱ በሚመድባቸው ወቅታዊ ሥራዎች ላይ የማገልገል፣
4.2.8 ቤተክርስቲያን እውቅና ባልሰጣቸው መንፈሳዊ ማኀበራት አባል መሆን የለበትም፣
4.2.9 የሰ/ት/ቤቱን እና የቤተክርስቲያኒቷን ነዋያተ ቅዱሳት የመጠበቅ እና የመንከባከብ ግዴታ አለበት፣
4.2.10 ማንኛውም አባል በተከለከሉ ቦታዎች ማለትም፡-
  • በመናፍቃን አዳራሽ ሲማር ወይም ሲያስተምር፣
  • ለመንፈሳዊ ሕይወት በማይስማሙ/አልባሌ ቦታዎች/፣
  • የቤተክርስትያንን ስም በሚያስነቅፍ ቦታዎች መገኘት የለበትም እንዲሁም
  • በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው ከተለዩ ስዎች ጋር ማንኛውም ዓይነት መንፈሳዊ ግንኙት ማድረግ የለበትም፣
  4.2.11 ማንኛውም የሰ/ት/ቤት አባል ሰ/ት/ቤቱ ሳይወክለው ወይም ሳይልከው፣
  • በማንኛውም ቦታ ሰ/ት/ቤቱን መወከል፣
  • በሰ/ት/ቤቱ ስም ማንኛውንም ዓይነት መርሐ ግብር መዘርጋት፣
  • በሰ/ት/ቤቱ ስም ዕርዳታ ማሰባሰብ፣
  • በሰ/ት/ቤቱ ስም ማስተማር እና ጽሑፎችን መበተን፣
  • የሰ/ት/ቤቱን መገልገያ ንብረቶች ማዋስ አይችልም፡፡
4.2.12 ማንኛውም አባል የሰ/ት/ቤቱን አንድነት የሚያፈርስ ተግባር መፈጸም የለበትም፡፡ እንዲሁም የቡድን ስሜት መፍጠር የለበትም፣
4.2.13 ከሰ/ት/ቤቱ የሚዋሳቸውን ንብረቶች በወቅቱ የመመለስ ግዴታ አለበት፣
4.2.14 ማንኛውም አባል ለሌሎች አባላት እንዲሁም ምዕመናን ማሰናከያ የሚሆን ነገር መሥራት የለበትም፣
4.2.15 ማንኛውም አባል ለፈተና የሚያጋልጡ እና ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ውጭ የሆነ አለባበስ፣ የተለያዩ ቀለሞች እና ጌጣጌጦች መጠቀም የለበትም፣
4.2.16 በሰ/ት/ቤቱ መደበኛ መርሐ ግብራት እንዲሁም በአውደ ምህረት ስብከት ወንጌል እየተሰጠ ተስብስቦ መቆም፣የግል ወሬ ማውራት እና የግል ሥራ መስራት የተከለከለ ነው፡፡
4.2.17 የስም መቆጣጠሪያው ላይ ስሙን የማስመዝገብ እና ምልክት የማስደረግ ግዴታ አለበት፣
4.2.18 ረጅም ጊዜ በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች ራቅ ብሎ የሚሄዱ አባል በሰ/ት/ቤቱ መርሐ ግብራት ለረጁም ጊዜ መካፈል የማይችል ከሆነ እስኪመቻችለት ድረስ በአባልነት ለመቆየት እንዲፈቀድለት የሚመለክተውን ክፍል መጠየቅ እና ፈቃድ ማግኘት አለበት፣
4.2.19 ማንኛውም የሰ/ት/ቤት አባል በሰ/ት/ቤቱ በሚካሄደው ሳምንታዊ መርሐ ግብርና  መደበኛ ተከታታይ ትምህርት እንዲሁም ሰ/ት/ቤቱ በሚጠራው ስብሰባ ላይ መቅረት የለበትም፣ የሚቀር ከሆነም ችግሩን በማመልከቻ ገልጾ ሲፈቀድለት መሆን አለበት፣
4.2.20 በተለያዩ ምክንያቶች ከሰ/ት/ቤቱ ለመልቀቅ የሚፈልግ አባል ሰ/ት/ቤቱን ከመልቀቁ በፊት የሚለቅበት ምክንያት በግልጽ በጽሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
4.2.21 ማንኛውም አባል ጋብቻውን መፈጸም ያለበት በሥርዓተ ቤተክርስቲያን መሆን አለበት
4.2.22 ማንኛውም አባል ከሰ/ት/ቤቱ አባላት ጋር ተቻችሎ መኖር አለበት፣
4.2.23 የሰ/ት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ የመጠበቅ፣




አንቀጽ 5
ከአባልነት የሚያሳግዱ ነጥቦች
5.1 የሌላ እምነት ተከታይ ሆኖ ሲገኝ፣
5.2 በቀሪ ብዛት የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ አልፎ ሲገኝ እና ሥራ አስፈጸሚው ሲያምንበት፣
5.3 የሰ/ት/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ተላልፎ ሲገኝ እና ሥራ አስፈጻሚው ሲያምንበት፣

                                 አንቀጽ 6
የአገልጋይ መብት እና ግዴታ
 6.1   የአገልጋይ መብት
6.1.1 ሰ/ት/ቤቱ በመደበው የአገልግሎት ክፍል የማገልገል፣
6.1.2 ሰ/ት/ቤቱ የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ካሟላ በተዋረድ ባሉ ክፍሎች በሥራ አስፈጻሚነት እና አባልነት የመመረጥ፣
6.1.3 በአሳማኝ ምክንያት ሰ/ት/ቤቱን ሲለቅ እና በጽሑፍ መልቀቂያ ሲጠይቅ መረጃ የማግኘት፣
6.1.4 ማንኛውም አገልጋይ በአገልጋይነቱ ሰ/ት/ቤቱ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም አይነት፣አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፣
6.1.5 አንድ አገልጋይ ከአገልግሎት ርቆ ቆይቶ መመለስ ቢፈልግ ለሥራ አስፈፃሚው አቅርቦ ሥራ አስፈፃሚው ካመነበት ወደ አገልግሎት ይመለሳል፡፡
6.1.6 አንድ አገልጋይ ከተመደበበት ክፍል በፈቃደኝነት አላገለግልም ብሎ በጽሑፍ ቢያቀርብ እና ሥራ አስፈጻሚው ካመነበት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
6.1.7 አንድ አገልጋይ በአገልግሎት የሚያጋጥሙትን ችግሮች በጽሑፍም ሆነ በቃል
        የማቅረብ መብት አለው፡፡
6.2 የአገልጋይ ግዴታ
6.2.1 አንድ አገልጋይ ለማገልገል ከጽ/ቤቱ የአገልግሎት ፈቃድ ማግኘት አለበት፣
6.2.2 አንድ አገልጋይ በተመደበበት የአገልግሎት ክፍል የማገልገል ግዴታ አለበት፣
6.2.3 አንድ አገልጋይ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለመምራት (አርአያ) ለመሆን ጥሩ የሥነ-ምግባር ባለቤት የመሆን ግዴታ አለበት፣
6.2.4 የሰ/ት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ የመጠበቅ፣
6.2.5 ሰ/ት/ቤቱ በሚያዘው የሥራ መስክ ሁሉ እንደ አቅሙ የመታዘዝ ግዴታ፣
6.2.6 ጥፋት አጥፍቶ ሲገኝ የሚሰጡትን የቅጣት ማስጠንቀቂዎች እንዲሁም ቅጣቶችን
        የመቀበል ግዴታ አለበት፣
6.2.7 የሰ/ት/ቤቱን ወርሀዊ አስተዋጽኦ የመክፈል ግዴታ አለበት፣
አንቀጽ 7
ለሥራ አስፈፃሚነት ለመመረጥ መሟላት ያለባቸው ነጥቦች፣
7.1 በኢ/ኦ/ተ/ ሃይማኖቱ ጽኑ የሆነ እና በግብረገብነቱ የተመሰከረለት
7.2 በሰ/ት/ቤቱ በአባልነት ቢያንስ ለ4 ዓመታት የቆየ፣
7.3 በሥራ አስፈፃሚነት አባል ለመሆን 2/3ኛ የሥራ አስፈፃሚ ድምጽ ማግኘት አለበት፣
7.4 ዕድሚያቸው ሃያ/20 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
7.5 ለአገልግሎት በቂ ጊዜ ያለው፣
7.6 የሰ/ት/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ጠብቆ ማስጠበቅ የሚችል፣
                            አንቀጽ 8
ከአገልጋይነት የሚያሳግዱ ነጥቦች፣

8.1 የሌላ እምነት ተከታይ ሆኖ ሲገኝ
8.2 የሰ/ት/ቤቱን ብሎም የአጥቢያውን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ፣
8.3 የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት ካልቻለ
8.4 ሰ/ት/ቤቱ ያወጣውን መተዳደሪያ ደንብ ማክበር እና በደንቡ መሰረት መመራት ካልቻለ፣
8.5 በቀሪ ብዛት የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች ተላልፎ ሲገኝ እና ሥራ አስፈፃሚው
      ካመነበት፣







አንቀጽ 9
የሰ/ት/ቤቱ መዋቅር እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
9.1 የሰ/ት/ቤቱ መዋቅር
 9 1 1 ሰ/ት/ቤቱ ተጠሪነቱ ለቤተክርስቲያኑ ሰበካ ጉባዔ ነው
 9 1 2 የሰ/ት/ቤቱ ሥራ አመራር ብዛታቸው ከ7-12 ሊደርስ ይችላል፡፡
     9 1 3 የሰ/ት/ቤቱ የሥራ አመራር (ሥራ አስፈፃሚ) ከዚህ በታ 
               የተዘረዘሩት ክፍሎች አሉት፡-
1 የሰ/ት/ቤቱ ሊቀመንበር እና ፀሐፊ (ጽሕፈት ቤት)
2 የሰበካ ጉባዔ ተወካይ
3 ትምህርት ክፍል
4 መዝሙር እና ሥነ-ጥበባት ክፍል
5 አባላት ጉዳይ ክፍል
6 ግንኙነት ክፍል
7 ልማት ክፍል
8 ሂሳብ እና ንብረት ክፍል
9 ሕፃናት ክፍል
10 በጎ አድራጐት ክፍል
11 መርሐ ግብር ክፍል
12 ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ክፍል

ማሳሰቢያ፡- ይህ መዋቅር እንደ አስፈላጊነቱ በጊዜው ባሉ ሥራ አስፈፃሚዎች ሊቀያየር እና ሊሻሻል ይችላል፡፡




                 9.2 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

9.2.1 ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ይሆናል፣
9.2.2 ከ7-12 አባላት ይኖሩታል፣
9.2.3 በጠቅላላ ጉባኤ ተመርጦ የሚሰየም ሲሆን ጠቅላላ የሰ/ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ይመራል፣
9.2.4 የሰ/ት/ቤቱን በጀት ያፀድቃል፣
9.2.5 በየሦስት ወሩ የሰ/ት/ቤቱን የስራ አፈፃፀም (ሪፖርት)ይገመግማል፣
9.2.6 የሰ/ት/ቤቱ ዓላማዎች መተግበራቸውን ይከታተላል፡፡
9.2.7 የሰ/ት/ቤቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከሚመለከተው አካል ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣
9.2.8 የሰ/ት/ቤቱን ተግባራት ለማከናወን የተለያዩ ዘዴዎችን ይቀይሳል፣
9.2.9 የሰ/ት/ቤቱን ዓላማና ተግባር ለማሳካት እንቅፋት የሚሆኑ ማንኛውንም አባልት ላይ የተለያዩ የማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ይወስዳል፣በዚህም የማይስተካከል ከሆነ ጉዳዩን ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ከአባልነት እንዲሰረዝ ያደርጋል፡፡
9.2.10 የሥራ አስፈፃሚ ከተመረጠበት አንስቶ ለ3 ዓመታት ያገለግላል፡፡






አንቀጽ 10
የሰ/ት/ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ ተግባር እና ኃላፊነት

10.1                                      የሰ/ት/ቤቱ ሊቀመንበር ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈፃሚ ሲሆን የሰ/ት/ቤቱ ጸሐፊ ተጠሪነቱ ለሰብሳቢ  ይሆናል፡፡ ሌሎች የሰ/ት/ቤቱ የሥራ አመራሮች ተጠሪነታቸው ለዚህ ጽ/ቤት ነዉ፡፡ እንደአስፈላጊነቱ ሰ/ት/ቤቱ ባመነበት ክፍሎችን በሰብሳቢ  እና በጸሐፊው የበላይነት እንዲመሩ ያደርጋል፡፡ አጠቃላይ ሥራ አስፈፃሚው ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ነዉ፡፡ የሥራ አስፈፃሚውን በሊቀመንበርነት የሚመራው የሰ/ት/ቤቱ ሰብሳቢ ነዉ፡፡ በአጠቃላይ በሥራ አስፈፃሚነት ተመርጦ የሚሰራ ሰው ቃል የገባውን ኃላፊነት ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ ታዛዥነትን በመቀበል የሰ/ት/ቤቱን ህልውና መጠበቅ አለበት፡፡ የእያንዳንዱ ክፍል ኃላፊነት እና ተግባር ከዚህ በታች በዝርዝር ይገኛል፡፡

10.1.1የሰት/ቤቱ ሰብሳቢ
ኃላፊነትና ተግባር
1      ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይሆናል፣
2      ከሰበካ ጉባዔ የሚተላለፉትን መመሪያዎች ተግባራዊ ያደርጋል፣
3      የሰ/ት/ቤቱን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በበላይነት ይመራል፣ ውሳኔውንም ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያስተላልፋል፣ተፈፃሚነታቸውንም ይከታተላል፣
4      ጽ/ቤቱን በተመለከተ ከፀሐፊው ጋር በመነጋገር አጀንዳዎች እንዲዘጋጁ ያዛል
5      የሰ/ት/ቤቱን ክፍሎች ጠቅላላ መርሐግብር እና እንቅስቃሴያቸውን ይከታተላል፣
6      ከተለያዩ ቦታዎች ለሰ/ት/ቤቱ የሚመጡትን ደብዳቤዎች በማስተናገድ አስፈላጊውን መልስ ይሰጣል ወይም ለሚመለከተው ክፍል በመምራት በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
7      ሰ/ት/ቤቱን በተመለከተ ከተለያዩ ቦታዎች ለሚመጡ የስብሰባ ጥሪዎች ሰ/ት/ቤቱን ውክሎ ይገኛል ወይም በተዋረድ የሚመለከተውን ክፍል እንዲሳተፉ ያዛል፣



8      አንድ ስራ አስፈፃሚ በሥራው ቢደክም፣መመሪያ እና ደንብ ባይጠብቅ፣በሥነ-ምግባር ብልሹ ቢሆን፤ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት ባይችል….ወዘተ ሰብሳቢ  

  • ይመክራል
  • በደብዳቤ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል
  • ካለው የሥራ ኃለፊነት እንዲወርድ የሥራ አስፈፃሚን ልዩ/መደበኛ ስብሰባ በመጥራት ያሉትን ችግሮች ለሥራ አስፈፃሚ በማቅረብ ስራ አስፈፃሚ ሲያምንበት ከሥራው/ከስራ አመራርነቱ እንዲታገድ ያፀድቃል፣
  • በድምጽ አሰጣጥ ስዓት የሰብሳቢ  ድምጽ ተቆጣሪነት ይኖረዋል፡፡
  • ሥራ አስፈፃሚው ያመነበትን ውሳኔ ለተወሰነበት ሰው በደብዳቤ እንዲገለጽለት ያደርጋል፣
9      የሰ/ት/ቤቱ የሥራ አስፈፂሚዎች በወጣው የሥራ መመሪያና ደንብ መሰረት መስራታቸውን ይቆጣጠራል፣
10    የሰ/ት/ቤቱ ሰብሳቢ ለአመቱ የወጡትን እቅዶች ከሥራ አስፈፃሚው ጋር በመሆን ተገምግመው በሥራ ላይ እንዲውሉ ያፀድቃል፣
11    ሰብሳቢ  የወጡትን እቅዶች መተግባራቸውን በመደበኛ እና እንደአስፈላጊነቱ ልዩ ስብሰባ  በመጥራት ተፈፃሚነታቸውን ይገመግማል፣ ውሳኔ ያስተላልፋል፣ያፀድቃል
12    ለሰ/ት/ቤቱ እድገትና መጠናከር ከሰ/ት/ቤቶችና ከቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ጋር በመነገጋገር ግነኙነት ይፈጥራል፣
13    ግማሽ እና ከግማሽ በላይ የሆኑ ስራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት ሰብሰባውን የማካሄድና የማስወሰን ኃላፊነት አለበት፣
14    በከፍተኛ የሂሳብ ሰነዶች ላይ ይፈርማል ከብር 100 በታች በቋሚ ውክልና ለፀሐፊው እንዲያፀድቅ በደብዳቤ ያዛል፣
15    ከሥራ አስፈፃሚ አቅም በላይ የሆኑ ጉዳዩች ሲያጋጥሙ ሰብሳቢ  ለሰበካ ጉባኤ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
16    በማንኛውም ስብሰባ ወቅት በውሳኔ አሰጣጥ በኩል እኩል ድምጽ በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳቢ  የደገፈው ሃሳብ ይፀድቃል፡፡

    10.1.2 የሰ/ት/ቤቱ ጸሐፊ
ኃላፊነት እና ተግባር
1 ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቱ ሰብሳቢ ይሆናል፣
2       የጽ/ቤቱን አጀንዳዎች ከሰብሳቢ  ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣
3      ለሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ መኖሩን በውስጥ ማስታወሻ እና በቃል ያሳውቃል፣
4የሰ/ት/ቤቱ የተለያዩ ክፍሎች እንዲቀርብላቸው የሰጡትን አጀንዳዎች በቅደም ተከተል እንደ አስፈላጊነቱ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
4        የጽሕፈት ቤት ሥራዎችን ከስብሳቢው ጋር በመሆን ያከናውናል፡፡
5      በእያንዳንዱ የስብሰባ እለት ቃለ ጉባዔ ይይዛል፣ ተሰብሳቢዎች እንዲፈርሙ ያደርጋል፣ የተወሰኑ ውሳኔዎች ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፣
6      በሰ/ት/ቤቱ ሥር ያሉትን የተወሰኑ ክፍሎችን በበላይነት ያገለግላል፣
7      በሰ/ት/ቤቱ መርሀ ግብር በመገኘት የዕለታዊ መርሐ ግብራት ይዘት ይቆጣጠራል፣
8      በሚመራቸው ክፍሎች የሥራ ድክመት ሲኖር ለሰብሳቢ  ሪፖርት በማድረግ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፣
9      ፀሐፊው ወጪን በተመለከተ ሰብሳቢ  እስከ 100 ብር ድረስ ቋሚ ውክልና ሲሰጠው
     በሰነድ  ላይ ይፈርማል፣
10 በበላይነት ሆኖ ከሚከታተላቸው ክፍሎች ያገኘውን የሦስት ወር ሪፖርት አጠቃሎ   
    ያቀርባል፣
11 ሰብሳቢ በሌለበት ጊዜ በውክልና ፀሐፊው የበላይ ሆኖ ይቆጣጠራል፣
12 የሰ/ት/ቤቱን ወጭ እና ገቢ ደብዳቤዎች በመዝገብ እየመዘገበ ያስቀምጣል፣
13 በስብሰባ ጊዜ ስብሰባው በስዓቱ እንዲጀምር እና እንዲቋጭ ያደርጋል/የስብሰባ ስዓት
    ይቆጣጠራል፣
14 በአስፈላጊ ጊዜ እና በሰ/ት/ቤቱ ዓመታዊ በዓል ላይ አጠቃላይ የሰ/ት/ቤቱን ሪፖርት አርቅቆ
    ያቀርባል፣
10 1 3 የስበካ ጉባዔ ተወካይ
ዓላማው
–   በሰበካ ጉባኤ ምርጫ ጊዜ የሰ/ት/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ሁለት እጩወች ያቀረርባል ዓላማውም ሰ/ት/ቤቱ ተጠሪነቱ ለስበካ ጉባዔ እንደመሆኑ በሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት በኩል ወደ ሰበካ ጉባዔ ዕውቅና እንዲኖራቸው የሚታዘዙ ጉዳዮችን፣ሰ/ት/ቤቱን ወክሎ ስብሰባዎችን፣እንዲሁም ከሰበካ ጉባዔ ወደ ሰ/ት/ቤቱ የሚመጡ ውሳኔዎችን ለሰ/ት/ቤቱ ማቅረብ እና ወዘተ.. የመሳሰሉትን በመሥራት የሰ/ት/ቤቱን ፍላጐት ማሟላት ናቸው፡፡

ተግባር፡-
1     ተጠሪነቱ ለበሰበካ ጉባኤ ይሆናል፣
2   ተወካዩ የሥራ አስፈፃሚው ያላመነበትን እና ያላፀደቀውን ጉዳይ ወደ ሰበካ ጉባዔ ሊወስድ አይችልም፣
3   ሰ/ት/ቤቱን ወክሎ በሰበካ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ይካፈላል፣ የሚሰጡ ውሳኔዎችንም ለጽ/ቤቱ በሰዓቱ ያቀርባል፣
4   ከሰ/ት/ቤቱ ወደ ሰበካ ጉባኤ የሚደርሱ አጀንዳዎችንና ሥራዎችን በሰዓቱ ያቀርባል፣
5   እነዚህን ተግባራት መፈጸም ካልቻለ የሰ/ት/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ በጽ/ቤት በኩል ለሰበካ ጉባኤ እንዲቀርብ ያደርጋል፣  

10 1 4 የሰ/ት/ቤቱ ሂሳብ እና ንብረት ክፍል
ሂሳብ ክፍል ተግባር እና ኃላፊነት
1    ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሆኖ የሚሰጡትን ተግባራት ይፈጽማል፣
2   የሰ/ት/ቤቱን ልዩ ልዩ ገቢዎች በጥንቃቄ ይይዛል፣ ለገቢ ሂሳቦች ደረሰኝ ይሰጣል፣
3   የገንዘብ ወጭ በሚጠየቅበት ጊዜ በሰብሳቢ  ወይም በፀሐፊው እስከተሰጠው ውክልና ድረስ በፊርማና በስም ካልፀደቀ ወጭ አይሆንም፣
4   ከወጪ ቀሪ የሚሆነውን ገንዘብ በትክክል ሰጠሁ ተቀበልኩ በሚል መዝገብ በመመዝገብ ባላንስን መቆጣጠር እንዲሁም ወጪ የተደረገባቸውን ሰነዶች በጥንቃቄ በመያዝ ማስቀመጥ፣
5    ማንኛውም ገንዘብ ባልተፈቀደለት ሰው ወጪ እንዳይሆንና እንዲሁም የገንዘብ ማስቀመጫው ቁልፍ እንዳይጠፋ ጥንቃቄ ማድረግ፣
6   የሰ/ት/ቤቱ ገንዘብ ሰብሳቢ ለገንዘብ ያዥ በሚያስረክብበት ጊዜ የመረካከቢያ መተማመኛ በመዝገብ በመፈረም መረከብ/በዚህ ስዓት የሰብሳቢው፣የገንዘብ ያዥና የፀሐፊ መተማመኛ ፊርማ መኖር አለበት፣
7   የሰ/ት/ቤቱን ገቢና ወጪ ለማወቅ ኦዲት ሊደረግ ሲያስፈልግ የሂሳብ መዝገብና ሰነዶችን በማቅረብ ያስመረምራል፣
8   የሰ/ት/ቤቱ ገንዘብ እንደመሆኑ መጠን ጉድለት ቢገኝ ያስጠይቃል፣
9   ወርሐዊ አስተዋጽኦ ከሰ/ት/ቤቱ አባላት ይስበስባል፣
  • አባላት ወርሐዊ አስተዋጽኦ እንዲከፍሉ ያበረታታል፣
  • በተጨማሪ በጽ/ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፣
ለ. የንብረት ክፍል ተግባር እና ኃላፊነት
1   ተጠሪነቱ ለሒሳብ እና ንብረት ክፍል ሁኖ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፣
2 ማንኛውንም ቋሚና አላቂ ዕቃ ተገዝቶ ሲመጣ ከሚያቀርበው ዝርዝር ደረሰኝ ጋር    እያመሳከረ ገቢ ያደርጋል፣
3     የሚወጣው ዕቃ አላቂና ቋሚ መሆኑን በደንብ በማረጋገጥ በሚቀርበው መጠይቅ ማስተናገድ
4     ዕቃ ወጪ እንዲሆን መጠየቂያ ሲቀርብለት ከሚመለከተው ክፍል ፈቃድ ማግኘቱን ያረጋግጣል፣
5     ያለውን ንብረት በመመዝገብ ወጪና ቀሪውን በማመሳከር ያለውን ንብረት ባላንስ በየጊዜው ማወቅ፣
6     ዕቃ ወጪ እንዲሆን ሲጠየቅ ከሚመለከተው ክፍል ሲፈቀድ በወጪ መዝገብ አስፈርሞ ይሰጣል፣
7     ማንኛውም ዕቃ ከደንብና መመሪያ ውጭ ገቢና ወጪ እንዳይሆን ይጠብቃል፣
8     ንብረትን በተመለከተ ጉድለት ወይም የአሰራር ብልሸት ቢፈጠር በኃላፊነት ያስጠይቃል፣
9     በዓመቱ የንብረት ቆጠራ ጊዜ የማስቆጠር ኃላፊነት አለበት፣
10    የተለየ አፈፃፀም ሲመጣ ከጽ/ቤቱ ሕጋዊ የሆነ ደብዳቤ ማግኘት አለበት፣

11.ንብረቶች ከጠፉ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለተጠሪው ሪፖርት ያደርጋል፣
12.ለንብረቶች መለያ ቁጥር ይሰጣል፣


            ሐ. መዝገብ ክፍል
1     ተጠሪነቱ ለሂሳብ እና ንብረት ክፍል ሆኖ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፣
2    ለሰ/ት/ቤቱ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በአግባቡ እና በጥንቃቄ በማስቀመጥ ዶክመንት ያደርጋል፣
3    ዶክመንት የተደረጉ መረጃዎች በአስፈላጊ ጊዜ ለሚመለከተው ክፍል በውሰት መልክ አስፈርሞ ይሰጣል፣
4    የተዋሱ ዶክመንት የነበሩ ንብረቶች በስዓቱ እንዲመለሱ ያደርጋል፣

መ ወርሐዊ አስተዋጽኦ ንዑስ ክፍል
1     ተጠሪነቱ ለሂሳብ እና ንብረት ክፍል ነው፡፡
2    ከአባላት ወርሐዊ አስተዋጽኦ ይሰባስባል፣ የሰበሰበውን ገዘብ ከመዘገበ በኋላ ለሂሳብ ክፍሉ ገቢ ያደርጋል
3    ወርሃዊ አስተዋጽኦ ያልከፈሉ አባላትን በመለየት እንዲከፍሉ ያደርጋል፣

10 1 5 በጎ አድራጎት ክፍል

ዓላማ፡- የበጎ አድራጎት ክፍል ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣የተቋቋመበት አላማ በሰ/ት/ቤቱ እና በአጥቢያው ለሚገኙ ምዕመናን የተለያዩ አገልግሎቶችን እና በጎ ሥራዎችን ለመስራት ሲሆን፣ይህ ዓላማው ተፈጻሚነት እንዲኖረው በውስጡ የውስጥ ርዳታ፣ የውጭ ርዳታ፣ ቲቶሪያል/ የማጠናከሪያ ትምህርት/፣ የአባላት ገቢ ኘሮጀክት ንዑስን ክፍሎች አሉት፣
ሀ. የውስጥ ርዳታ ንዑስ ክፍል፡
1   ተጠሪነቱ ለበጎ አድራጎት ክፍል ነው
2   በሰ/ት/ቤቱ እና በቤተክርስቲያኒቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ያሉትን አገልዮች እና  መገልገያ ንዋያትን አስፈላጊውን ርዳታ እና እንክብካቤ ማድረግ፣
3   የሰ/ት/ቤቱን እና የቤተክርስቲያኒቱን ንጽህና መጠበቅ
4   ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮች እና የሰ/ት/ቤቱን አባላት አስፈላጊውን እርዳታ እንዲደረግላቸው ማሳወቅ፣
የስ/ት/ቤቱ ግንኙነት ክፍል
ዓላማ
  • ወደ ስንበት ት/ቤቱ በተለያዩ መንገዶች የሚመጡ እንግዶችን በመቀበል አስፈላጊውን መስተንግዶ ያደርጋል
  • መንፈሳዊና ታሪካዊ ቦታዎች እንዲጎበኙ ደርጋል፣
የክርስቲያን አገናኝ ክፍል አላማውን ለመፈፀም ሶስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን
እነርሱም፡-
1. አዳዲስ አባላት
2. የውጭ ግንኙነት
1. የክርስቲያን አገናኝ ዋና ክፍል
ተግባር፡-
1.1.  ተጠሪነቱ ለፀሐፊ ሆኖ የሚሰጡትን መመሪያ፣ ደንብ፣ የስራ የተግባራት ይፈፅማል፣
1.2.  የክፍሉን ስራ በበላይ ሆኖ ይቆጣጠራል፣
1.3.  ለሰንበት ት/ቤቱ በተለያየ መንገድ የሚመጡ እንግዶችን በመቀበል ለተገቢው ክፍል በማስተዋወቅ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፣
1.4.  ለሰንበት ት/ቤቱ አዲስ የሆኑ እንግዳ አባሎች ተገቢውን ትምህርት ማግኘታቸውን ይቆጣጠራል፣ 
1.5.  እንግዳ አባላት የተሰጣቸውን የሰ/ት/ቤት ቀዳማይ ኮርስ እንደጨረሱ የተማሩትን መረዳታቸውን ለማወቅ ፈተና ተዘጋጅቶ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣
1.6.  አዲስ እንግዳ አባላት የሰ/ት/ቤቱን ኮ/ርስ/ትምህርት/ እንደጨረሱ በእሁድ ፕሮግራም እንዲመረቁ ያደርጋል
1.7.  አንድ የሰ/ት/ቤት አባል ወይም ከሌላ ሀገር ሰ/ት/ቤት ሲመጣ በእንግድነት ተቀብሎ አባል የመሆን ፍላጎት ካለው ከመጣበት ቦታ ህጋዊ የሆነ የመሸኛ ደብዳቤውን በመቀበል አባል እንዲሆን ለጽ/ቤቱ በመግለፅ ያመጣውን ደብዳቤ ፎቶ ኮፒ በማድርግ ከማህደሩ ጋር እነዲያያዝ /ለሚመለከተው ክፍል ያስተላልፋል/
1.8.  ማንኛውም የሰንበት ት/ቤቱ አባል ወይም ሌላ አካል በሰ/ት/ቤቱ ስም የክርስቲያን አገናኙ ክፍሉ ሳያውቀው እንግዳ አባላትን ተቀብሎ እንዳያስተምር ይቆጣጠራል፣
1.9.  የግንኙነት ክፍሉ በመሸኛ ጊዜ፣ በምረቃ ጊዜ፣ በሠርግና ከተለያዩ ሀገሮች የሚመጡ እንግዶችን በመቀበል ያስተናግዳል ለዚህም ጉዳይ የሚፈለገውን ነገር ከጽ/ቤቱ ይጠይቃል፡፡
1.10.          የግንኙነት ክፍሉ የተለያዩ መንፈሳዊ ጉዞዎች እንዲኖሩ ከጽ/ቤቱ ጋር በመሆን ያመቻቻል፣
1.11.          በሰ/ት/ቤቱ አባላት የደስታም ሆነ የሀዘን ወቅት እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ አባላት ለስራ እንዲሳተፉ ያደርጋል ማህበሩም በሚጠይቀው ትዕዛዝ ሁሉ ይሳተፋል፣
1.12.          የግንኙነት ክፍሉን ስራ በየወሩ ከክፍሉ ጋር ሆኖ ይገመግማል በየ እሩብ አመቱ በፅሁፍ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ያቀርባል፣
1.13.          ከጽ/ቤቱ ከስራው ድርሻ በተጨማሪ የሚታዘዘውን ስራ የግንኙነት ክፍሉ እንዲፈፅም ያደርጋል፣
1.14.          ለአዲስ አባላት የንስሀ አባት ለሌላቸው የንስሀ አባት እንዲይዙ ከሚመለከተው ክፍል ጋር ይነጋገራል፣
1.15.          ለአዲስ አባላት ከክርስቲያን አገናኙ ተገቢውን ትምህርት ተሰጠቷቸው አባል እስከሚሆኑ ድረስ ስማቸውን መዝግቦ በሰንበት ት/ቤቱ መርሃ ግብር መገኘታቸውን መቆጣጠር፣


የውጭ ግንኙነት
ተግባር
2.1.  ተጠሪነቱ ለግኝኙነት ክፍሉ ሆኖ የሚሰጡትን መመሪያ፣ የስራ ተግባር ይፈፅማል፣
2.2.  በግንኙነት ክፍሉ የሚሰጡትን ከተለያየ ሀገርና ሰ/ት/ቤት የሚመጡ ደብዳቤዎችን መልስ በመስጠት አገልግሎት፣ እርዳታ፣ ለሰ/ት/ቤቱ የሚጠቅሙ ነገሮችን በመፃፃፍ ይፈፅማል፣ ለሚመለከተው ክፍል ይሰጣል ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፡፡
2.3.  የተለያዩ ታሪካዊና መንፈሳዊ የሆኑ ቦታዎች እንዲጎበኙ ፕሮግራሞችን ከግንኙነት ክፍሉ ጋር በመሆን ያወጣል፣
2.4.  ከጽ/ቤቱ የሚታዘዘውን ተጨማሪ ስራ ይሰራል፣
2.5.  ከተለያ ስ/ት/ቤት ግቢ ጉበአያት እና መንፈሳዊ ማህበራት ግንኙነት በማድረግ ለስ/ት/ቤት እንደ ልምድ ልውውጥ ያደርጋል፡፡
የመዝሙር ስነ-ጥበባት
“በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊ ቅኔ እረስ በራሳችሁ ተነጋገሩ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ”
ኤፌ.ም 5 ቁ 19
“በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በፀጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ “ቆላ. ም. 3 ቁ 16
ዓላማ፡-
  • የሰ/ት/ቤቱ አባላት ልዩ ልዩ ያሬዳዊ መዝሙራትን የሚማሩበት፣ የሚደርሱበትና የሚያስተላልፉበት መንገድ መስጠትና በመዝሙር አማካይነት መንፈሳዊ መልዕክትን ማስተላለፍ ነው፡፡
  •  
ተግባር፡-
  1. 1.         የመዝሙር ክፍል አብይ የስራ መመሪያ
1.1.  የመዝሙር ክፍሉ ተጠሪነቱ ለ ጽ/ቤቱ ሆኖ የሚሰጡትን መመሪያ፣ ደንብ፣ የስራ ተግባራት ይፈፅማል፣
1.2.  የመዝሙር ክፍሉ ጽ/ቤቱ በሰጠው መመሪያ መሰረት የተፈቀዱ መዝሙሮችን እንዲዘምሩ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል፣
1.3.  በሰ/ት/ቤቱ መደበኛ በሆኑ መርሐ ግብራት ላይ በሚሰጠው መዝሙር እንዲቀርብ አገልግሎት እንዲፈፅሙ ያደርጋል፡፡
1.4.  መዝሙር ክፍሉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ስራ አስፈፃሚ ጋር በመነጋገር ወደ ሌሎች ሰ/ት/ቤቶች ለአገልግሎት ከወኪል ጋር ይላካል፣
1.5.  የመዝሙር አገልግሎት በደስታ እና በሀዘን ጊዜ ጽ/ቤቱ ለመዝሙር ክፍሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሲሰጠው ይፈፅማል፣
1.6.  መዝሙር ክፍሉ የሚዘምሮቸውን መዝሙሮች በጥራዝ መልክ በማዘጋጀት አባላት እንዲገለገሉበት አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ፣
1.7.  መዝሙራትን ወቅታቸውን ተከትለው እንዲዘምሩ የመዝሙር ክፍሉ በየወቅታቸው መሰብሰብና ለአገልግሎት እንደየአስፈላጊነቱ ማቅረብ፣
1.8.  ሰ/ት/ቤቱ መዘምራን በመዝሙር ጥናት ጊዜ ተገኝተው ልምምድ ማድረጋቸውን መቆጣጠር፣
1.9.  መዝሙር ክፍሉ የመዝሙር የሰው ኃይል ከበዛ በቡድን በመከፋፈል ለአገልግሎት እንዲበረቱ መንፈሳዊ የሆኑ ትጋቶችን በመፍጠር ጠንካራ አገልጋዬችን መፍጠር፣    
1.10.          መዝሙር ክፍሉ በየወሩ የክፍሉን ስራ ይገመግማል በየሩብ ዓመቱ በፅሁፍ ሪፖርት ያደርጋል፣/ ክፍሉ የስራ ሪፖርቶችን በሚያቀርብበት ወቅት በዓመቱ ሊሠራቸው ካሰባቸው እቅዶች ውስጥ ያከናወነውን፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና ለወደፊት ለመስራት መፍትሔ የሚሆኑ ሀሳቦችን ማካተት አለበት አለበት/
1.11.          የመዝሙር መገልገያ እቃዎች እንዲሞሉ መጣርና ያሉትንም በጥንቃቄ መጠቀም፣
1.12.          በሥራ አስፈጻሚ የፀደቀ ውስጠ ደንብ ይኖረዋል፣

ሥነ – ጥበባት ክፍል
ዓላማ፡-
  • የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ስርዓትን ባህልን ለወጣቱ በቲያትር፣ በሥነ – ፅሁፍና በመሳሰሉት አማካኝነት ትምህርት ሰጭ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የሰ/ት/ቤቱ  አባላት መንፈሳዊ ህይወት መቆጣጠር የኪነጥበብን ችሎታ ማዳበር፣
  • የሰ/ት/ቤቱ አባላት በመንፈሳዊና በስጋዊ የእውቀት አድማሳቸው እንዲሰፋ የተለያዩ ጽሑፎችን በማዘጋጀት አገልግሎት መስጠት፣
የኪነ-ጥበብ ክፍል  አላማውን ለመፈፀም ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን
እነርሱም፡-
1. የስነ – ጽሑፍ ንዑስ ክፍል፣
2. ድራማ
1. የስነ – ጽሑፍ ንዑስ ክፍል
ተግባር፡
1.1.  የኪነጥበብ ክፍል ተጠሪነቱ ጽ/ቤት ሆኖ የሚሰጡትን መመሪያ፣ ደንብና የስራ ተግባራት ይፈፅማል፣
1.2.  በሰንበት ት/ቤቱ ወይም በመ ንፈሳዊ ጉባኤዎች ሚቀርቡ ስነ – ጽሁፍ፣ ድራማና የመሳሰሉትን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓትና ደንብ አካያ ዝግጅቶችን ሳንሱር ያደርጋል፣ /እንዲደረጉ ያደርጋል/
1.3.  በዚህ ክፍል የሚደረጉ ከላይ ተጠቀሱ ዝግጅቶች እንደይዘታቸው ሳንሱር ለማድረግ ክፍሉ ችግር ካለበት ለሚመለከተው ክፍል የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
1.4.  ትላልቅ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ለምሳሌ ቲያትሮች፣ ከመታየቱ በፊት ከክፍሉ በተጨማሪ የሚመለከተው ክፍል ማየት አለበት፣
1.5.  በዓመታዊ በእለታዊና በትላልቅ መርሃ ግብሮች ወቅት እንደ አስፈላጊነቱ ለመርሃ ግብሩ ቲያትሮችና ግጥሞችን በማዘጋጀት ማቅረብ፣
1.6.  ለሰ/ት/ቤቱ መበደኛ መርሃ ግብር እንደ አስፈላጊነቱ ትምህርት ሊሰጡ የሚችሉ ቲያትሮችን ግጥሞችንና  ወዘተ ለአባላት እንዲያዘጋጁ ቅስቀሳ ማድረግ፣
1.7.  በኪነ – ጥበብ ክፍል የሚቀርቡ ስነ – ጽሁፍና መጽሔት ወዘተ ጽሁፍች ለሰ/ት/ቤቱ በማህደር በማስቀመጥ ለሚመለከተው ክፍል ይሰጣል፣
2. የድራማና የመድረክ ንዑስ ክፍል
2.1.  ተጠሪነቱ ለኪነጥበብ ክፍል ይሆናል፣
2.2.  በድራማ ወይም በመድረክ ዝግጅት ጊዜ የሚፈለገውን ነገር በመጠየቅ/ በማዘጋጀት ለድራማውና ለመድረኩ ውበት ይሰጣል፣
2.3.  ይህ ክፍል በሰ/ት/ቤቱ ስም በሚዘጋጀው ድራማ ከመድረክ ዝግድት አንስቶ ድራማን በበላይ ሆኖ በማሰልጠን የተዋጣለት ስራ እንዲሰራ ያደርጋል፣
2.4.  ለሰ/ት/ቤቱ ካሉት የገቢ ምንጭ ማስገኛ አንዱ ስለሆነ በአመቱ ሊያሳያቸው ካቀደው ድራማ በጥሩ ውጤት በመስራት ሰ/ት/ቤቱን የገንዘብ አቅም ያጎለብታል፣
2.5.  የድራማና መድረክ ንዑስ ክፍል ለድራማ ከንብረት ክፍል በማስፈቀድ ያወጣል፣
2.6.  ለድራማ የሚያስፈልጉ ነገሮች በሰ/ት/ቤቱ ከለሉ እንዲገዙለት በፅሁፍ አስቀድሞ ይጠይቃል፣
2.7.  ለድራማ ወጪ ያደረጋቸውን ንብረት ለንብረት ክፍሉ ገቢ ያደርጋል
2.8.  ድራማ በሚዘጋጅበት ጊዜ የኪነጥበብ ክፍሉ ሰ/ት/ቤቱን አገልጋይ በሚፈልግበት ቦታ ለአገልግሎት ያሰማራል፣
1. የትምህር ክፍል
ዓላማ፡
የትምህር ክፍል አላማ ወጣቶች የቤተክርስቲያንን ህግና ስርዓት ቃለ እግዚአብሔርን በመማር ወላጆቻቸውንና ታላቆቻቸውን አክባሪዎች እንዲሆኑ፣ በስነ-ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ፣ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በሚገባ አውቀው በሃይማኖት ትምህርት ብስለት እንዲያገኙ፣ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎችና እንዲሁም በአገልግሎት የሚታቀፉና የኃላፊነት ስሜት አቅም እንዲገነቡ ለማድረግ ሲሆን ይህ የትምህርት ክፍል ተጠሪነቱ ለፀሐፊው ሆኖ የሚከተሉትን ስራ ተግባራት ይፈፅማል፡፡
1.1.  በትምህርት ክፍሉ ስር የሚገኙ ንዑሳን ክፍሎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በትክክል መወጣታቸውን /መስራታቸውን/ ያረጋግጣል መመሪያ ያስተላልፋል፣
1.2.  ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ 3 / ሦስት/ ወር አንድ ጊዜ የክፍሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል፣
1.3.  የአመቱን ድርጊዘት መርሃ ግብር በማጥናት ለጽ/ቤቱ ያቀርባል፣
1.4.  የትምህርት ንዑሳን ክፍሎችን በአጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በየወሩ ይገመግማል፣
1.5.  የትምህርት ክፍሉ ከጽ/ቤቱ ትዕዛዝ ሲሰጠው ከአጥቢያ ቤተክርስቲያንና ከሌሎች ሀገሮች ሰ/ት/ቤቶች ትምህርት ክፍል ጋር የስራ ልምድ ልውውጥ በማድረግ በተፈፃሚነቱ ጥረት ያደርጋል፣
1.6.  በመደበኛ መርሃ ግብር ፕሮግራም በሰ/ት/ቤቱ ዕውቅናና ድጋፍ ካላቸው መመህራን ውጭ ተጋባዥ መምህራን  ሲመጡ ቀጥታ ወደ መርሃ ግብሩ እንዲቀርቡ ከማድረጉ በፊት ጉዳዩን ለጽ/ቤቱ ያሳውቃል ድጋፍ ሲገኝ መምህሩ ትምህርት እንዲሰጥ ይጋብዛል፣
1.7.  በሰ/ት/ቤቱ መርሃ ግብር በስብከት ትምህርትና በተከታታይ ትምህርት ለሚያገለግሉ መምህራን በሙሉ ከጽ/ቤቱ በሚገኘው የፕሮግራም ቅንጅት ድጋፍ ከአራት ወር አንድ ጊዜ መምህራኖችን በማሰባሰብ እንዲበረታቱና ለሰ/ት/ቤቱ መጠናከር የበኩላቸውን ድጋፍ እዳያቋርጡ ልዩ ፕሮግራም ይይዛል፣ በፕሮግራሙም ሰ/ት/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ኮመቴ ሚገኝበት ይሆናል፡፡
1.8.  የትምህርት ክፍሉ ንዑሳን ክፍሎችን በወር አንድ ጊዜ ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አመችነት ባለው በማንኛውም ጊዜ ይሰበስባል፣
1.9.  ከሰ/ት/ቤቱ የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሆን ያደርጋል፣
1.10.          ክፍሉ ስራና ኃላፊነት በተጨማሪ በጽ/ቤቱ የሚሰጠውን ተግባራት ይፈፅማል፣
2. መምህራን ምደባ ንዑስ ክፍል
2.1.  በመደበኛ የሰ/ት/ቤት ሳምታዊ መርሃ ግብር ፕሮግራም መምራንን ይመድባል
2.2.  ከሰ/ት/ቤቱ መደበኛ ፕሮግራም ውጭ በሰ/ት/ቤቱ ስርና እውቅና ኖሮአቸው ለሚካሄዱ መርሃ ግብሮች /ምሳሌ በፃድቃን ወይም በመላዕክት ስም በሚቋቋሙ የፅዋ ማህበራት፣ በአገልጋዩች ልዩ የመርሃ ግብር ወዘተ/ እንደአስፈላጊነቱ መምህራን እንዲመደቡ ያደርጋል፣
2.3.  በሰ/ት/ቤቱ እውቅና የሌላቸው እንግዳ መምህሮች ሲመጡ ይህ ክፍል እንዲያስተምሩ ከመጋበዝ በፊት ለትምህርት ክፍሉ ያሳውቃል ድጋፍ ሲያገኝ እንዲያስተምሩ ፕሮግራም ያመቻቻል፣
2.4.  የስብከት ትምህርት እንደአስፈላጊነቱ በድምጽ እና በምስል እንዲሰጥ ያመቻቻል፣
2.5.  ተጠሪነቱ ለትምህርት ክፍል ይሆናል፣
3. የተከታታይ ትምህርት ንዑስ ክፍል
3.1.  ለሰ/ት/ቤቱ አባላት እና በጥቢያው ለሚገኙምዕመናን በአመቱ ውስጥ ተከታታይ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት እንዲያገኙ ፕሮግራም ያመቻቻል፣
3.2.  እንደ አስፈላጊነቱ በመደበኛ የእሁድ መርሃ ግብር ለጉባኤው ተከታታይ ትምህርት እንዲሰጥ ያደርጋል፣
3.3.  ለሰ/ት/ቤቱ አገልጋዬች የሚመጥንና ለአገልግሎት እንዲበረቱ ተከታታይ የሆነ መሠረታዊ ትምህርቶች እንዲሰጥ ያደርጋል፣
3.4.  መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለተወሰኑ ብስለት ላላቸው አገልጋዬች ለረዥም ጊዜ መርሃ ግብር በማመቻቸት ለሰ/ት/ቤቱ የሰባኪ ወንጌል አገልጋዬችን ለማፍራት ጥረት ያደርጋል፣
3.5.  ተጠሪነቱ ለትምህርት ክፍሉ ይሆናል፡፡
4. የጽሁፋዊ ትምህቶች ዝግጅት ንዑስ ክፍል
4.1.  በሰ/ት/ቤቱ ሳምንታዊ መደበኛ መርሃ ግብር የሚሰጠውን ትምህርትም ሆነ ስብከት መዝግቦ ያስቀምጣል፡፡ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ለአባላቱ የሚደርስበትን መንገድ ማጥናትና ጥናቱን ለጽ/ቤቱ እንዲቀርብ ማድረግ፣
4.2.  በአመቱ ውስጥ ለአባላትም ሆነ ለአገልጋዬች የሚሰጠውን ተከታታይ ትምህርት ትምህርቱን ከሚሰጡ መምህራን ጋር በመነጋገር የትምህርቱን ኮፒ ለሰ/ት/ቤቱ ተቀማጭ ዶክመንት ያስቀምጣል፣
4.3.  በሰ/ት/ቤቱ ስም ለሚዘጋጁ በራሪ ወይም ተቀማጭ ታሪካዊ ልዩ ፅሁፎች ዝግጅት ድርሻውን ይወጣል፣
4.4.  ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመተባበር በዕድሜ ደረጃ መምህራንን የሚጠቅም የመማሪያና ማስተማሪያ ፅሑፍ ማዘጋጀት፣
4.5.  አስፈላጊው በሆኑ ረዕሶች ፁሁፎችን ማዘጋጀት አሳርሞና የገደሉትን እንዲሟሉ በማድረግ በሚያመች መንገድ መድረስ፣
4.6.  ተጠሪነቱ ለትምህርት ክፍል ይሆናል፡፡
5. የጥናት የጥያቄና መልስ ትምህርት ንዑስ ክፍል
5.1.  መሠረታዊ የሆኑ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት የሰ/ት/ቤቱን አባላት በሙሉ በማሳተፍ የቃልና በፅሁፍ የሚሳተፉበትን መርሃ ግብር ያዘጋጃል፡፡ ከፈተና በኋላም መልሱን ለአባላቱ ያቀርባል በዓመቱ መጨረሻ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በሰ/ት/ቤቱ አመታዊ በአል ቀን በጥያቄው በተከታታይ ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላገኙ ሽልማት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
5.2.  በሰ/ት/ቤቱ በሚዘጋጁ ተከታታይ ትምህርትና እለታዊ ስብከት ርዕስ በመመስረት ጥያቄዎች አዘጋጅቶ አባላቱን በፈተና እያወዳደረ የተማሩትን እንዲያስታወሱ ያደርጋል እንደአስፈላጊነቱ የሽልማት ስጦታ ለአሸናፊው ያዘጋጃል፡፡
5.3.  በሰ/ት/ቤቱ ልዩ መርሃ ግብር ጥያቄና መልስ ውድድር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ያቀርባል፣
5.4.  ከአባላት በተለያዩ ጊዜያት የሚቀርቡ ትምህርታዊ ጥያቄዎችን ከመምህራን ጋር በመ ነጋገር መልስ ያቀርባል፡፡
5.5.  ቤጊዜው የሚዘጋጃቸውን ጥቄዎች ከነመልሳቸው በማህደር ያስቀምጣል ተባዝቶ መታደል የሚገባው ሲሆን ለጽ/ቤቱ በትምህርት ክፍሉ በኩል እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡
5.6.  ተጠሪነቱ ለትምህርት ክፍል ይሆናል፣




አባላት ጉዳይ ክፍል
ዓላማ
የአባላት ጉዳይ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ሆኖ አበላትንና በአገልግሎት ላይ ያሉ አገልጋዬች የሰ/ት/ቤቱን ደምብና መመሪያ እነደዲያከብሩ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰ/ት/ቤቱ አባላትና አገልጋዬች ህይወታቸው በቤተ ክርስቲያን ሆነ በአካባቢያቸው ክርስቲያናዊ ህይወት የተስተካከለ ስነ ምግባር ይኖራቸው ዘንድ ይመክራል ያስተምራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ በአጠቃላይ ሰ/ት/ቤቱ ይጥሩ ስነ ምግባር ማፍሪያና አባላት መልካም ህይወት ያላቸው በፍቅርም የሚኖሩ ይሆኑ  ዘንድ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

እነዚህን ተግባራት ለማከናወን አባላት ጉዳይ  ክፍሉ ሶስት ንዑሳን ክፍሎች ይኖሩታል፣
1. የአባላት ክትትል
2. የምክክር አገልግሎት
3. ስም ቁጥጥር
4. ጥናት
5. ንስሀ ክፍል
ተግባር፡-
  1. 1.         የአባላት ክትትል
1.1.  ለሰ/ት/ቤቱአባላት የአባልነት ፎርም ያዘሃጃ እንዲሁም አንዲሞሉ ያደርጋል 
1.2.  በሰ/ት/መርሃ ግብርና በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የአባላትን አባላት ጉዳይ  መቆጣጠር፣
1.3.  በሰ/ት/ቤቱ በአገልግሎት የተሰማሩ አገልጋዬች የሚታይባቸውን ጥፋቶች በክፍላቸው ለአንድ ጊዜ ምክር እንዲሰጣቸው ማድረግና ምክር የተሰጣቸው አገልጋዬች ጥፋታቸውን ማረማቸውን ማረጋገጥ፣
1.4.  የሰ/ት/ቤቱን አባላት ከቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውጭ ያለውን ህይወታቸውን መከታተል፣
1.5.  በአባለት ህይወት ችግር በተከሰተ ጊዜ ወዲያውኑ ለምክር አገልግሎት ንዑስ ክፍል ማቅረብ፣
1.6.  በክፍሉ ያከናወናቸውን ስራዎች በየጊዜው ለክፍሉ ተጠሪ ሪፖርት ማቅረብ፣
1.7.  ሰ/ት/ቤቱን ወክለው ለተለያዩ አገልግሎት ወደ ሌላ ሰ/ት/ቤት እና አገልግሎት የሚሄዱትን ልጆች ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር መርጦ መላክ፡፡
1.8.  በተጨማሪ የክፍሉ ኃላፊ የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮች ማከናወን
1.9.  በትምህርት ክፍል ውስጥ ያሉ አገልጋዬች ስነ – ምግባር ጉድለት ሲያሳዩ፣ ሰ/ት/ቤቱን ደንብ ሲተላለፉ ወይም የስ ድክመት ሲያሳዩ በሰ/ት/ቤቱ ደንብና መመሪያ መሠረት የእርምጃ ውሳኔ ያስተላልፋል፣
1.10.     አባላት በመካከላቸው መንፈሳዊ ህብረት፣ መተሳሰብና አንዳቸው ላንዳቸው ፍቅር እንዲኖራቸው ያደርጋል፣
1.11.     ተጠሪነቱ ለአባላት ጉዳይ  ክፍል ይሆናል፡፡

  1. 2.         የስም ቁጥጥር ንዑስ ክፍል ተግባርና ኃላፊነት
2.1.  በሰንበቱ ማንኛው ት/ቤቱ መርሀ ግበሮች ስም መቆጣጠር
2.2.  በሰ/ት/ቤቱመርሀ ግበሮች ለሶስት ተከታታይ ሳምንት የቀሩ አባላትን እንዲጠየቁ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያደርጋል፣
2.3.  በቀሪ ምክንያት ተጠይቀው እንደገና በአራት ተከታታይ መርሀ ግብሮች የቀሩ አባላትን ለአባላት ጉዳይ ክፍሉ አሳውቆ ተገቢውን መፍትሔ መስጠት፣
2.4.  የስብሰባቸው አቴንዳሶች ለሚመለከተው ክፍል ያስረክባል
2.5.  በሀዘንና በደስታ ጊዜ የሰ/ት/ቤቱ አባላት እንዲገኙ ማድረግ፣
2.6.  ተጠሪነቱ ለአባላት ጉዳይ ክፍሉ ይሆናል፡፡



  1. 3.         የምክክር አገልግሎት ንዑስ ክፍል ተግባርና ኃላፊነት፣

3.1.  በሰንበት ት/ቤቱ መካከል ቅሬታ ወይም ቂም ካለ በቀል ያላቸውን ጠርቶ በማነጋገር ቅሬታዎች እንዲወገዱ ትምህርትና ምክር መስጠት እንዲሁም አቅርቦ ማወያየት፡፡ አገልጋዬች ከሆኑ በክፍላቸው ለአንድ ጊዜ እንዲመከሩ ማድረግና ጥፋታቸውን የማያርሙ ከሆነ በሚያገኘው መረጃ መሰረት ምክር መስጠት፣
3.2.  ምክር የተሰጣቸውን አባላት ለወደፊቱ በጥፋት እንዳይገኙ ለማድረግ በሚዘጋጀው የማስፈረሚያ ቅጽ ላይ ማስፈረም፣
3.3.  ከአባላት ክትትል ንዑስ ክፍል በተከሰተባቸው የህይወት ችግር ምክንያት የሚመጡትን አባላት ተገቢውን ትምህርትና ምክር እንዲሰጣቸው ማድረግ
3.4.  በአገልጋዬችና በአባላት መካከል መለያየትና አለመግባባት እንዳይፈጠር ክትትል ማድረግ /አባላት ክትትል/
3.5.  በአጠቃላይ ከክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ውጭ የሆኑ አባላትንና አገልጋዬችን ምክር መስጠት፣
3.6.  ከሶስት ጊዜ በላይ ምክር የተሰጣቸውን አባላት ለአባላት ጉዳይ ክፍሉ ሪፖርት ማድረግ፣
3.7.  ተጠሪነቱ ለአባላት ጉዳይ ክፍሉ ይሆናል፡፡
  1. 4.         ንስሀ ክፍል
4.1.  የሰ/ትቤቱ አባላት የንስሀ ህይወት እንዲኖራቸው ያደርጋል
4.2.  የንስሀ አባላት የሌላቸውን የንስሃ አባት ያስይዛል
4.3.  ለንስሀ ዘሪያ የተለያዩ ጉባኤዎችን እና ጉዞዎችን ለአባላት ያዘጋጃል
4.4.  የሰ/ት/ቤቱ እንግዳ አባላት የትምህርት ጊዜያቸውን እንደጨረሱ ንስሀ እንዲገቡ ያበረታታል፣ የንስሀ አባት ከሌላቸው በማስያዝ እንዲገለገሉ ይመክራል ያስዋውቃል፣


  1. 5.         ጥናት ንዑስ ክፍል
5.1.  ገንዘብ ማስገኛ ከሆኑ ጥናቶች ውጭ በሰ/ት/ቤቱ  የታመነባቸውን ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል
5.2.  ያጠናቸውን ጥናቶች ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያደርጋል፡፡

የንብረት ክፍል
ተግባርና ኃፊነት
1. ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ሆኖ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፣
2. ማንኛውንም ቋሚና አላቂ ዕቃ ተገዝቶ ሲመጣ ከሚያቀርበው ዝርዝር ደረሰኝ ጋር እያመሳከረ ገቢ ያደርጋል፣
3. የሚወጣው ዕቃ አላቂና ቆሚ መሆኑን በደንብ በማረጋገጥ በሚቀርበው መጠይቅ ማስተናገድ
4. ዕቃ ወጪ እንዲሆን መጠየቂያ ሲቀርብለት ከሚመለከተው ክፍል ፈቃድ ማግኘቱን ይመለከታል፣
5. ያለውን ንብረት በመዝገብ ወጪና ቀሪውን በማሰከር ያለውን ንብረት ባላንስ በየጊዜው ማወቅ፣
6. ዕቃ ወጪ እንዲሆን ከሚመለከተው ክፍል ሲፈቀድ በወጪ መዝገብ አስፈርሞ ይሰጣል፣
7. ማንኛውም ዕቃ ከደንብና መመሪያ ውጭ ገቢና ወጪ እንዳይሆን ይጠብቃል፣
8. ንብረትን በተመለከተ ጉድለት ወይም የአሰራር ብልሽጽ ቢፈፀር በሃላፊነት ያስጠይቃል፣
9. በአመቱ የንብረት ቆጠራ ጊዜ የማቆጠር ኃላፊነት አለበት፣
  1. 10.         የተለየ አፈፃፀም ሲመጣ ከጽ/ቤቱ ህጋዊ የሆነ ደብዳቤ ማግኘት አለበት፣
በጎ አድራጎት ክፍል
ዓላማ፡
ሰንበት ት/ቤቱ በሚያስፈልገው የሞያ ነክ ሥራዎች ሁሉ ለማሰራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በማዘጋጀት በማህበሩ ውስት ያሉትን አባላት እንደየችሎታቸወው እንዲሰማሩ በማድረግ ቤተክርስቲያኒቱን ባላቸው የሞያ ችሎታ እንዲረዱ ማድረግ፣
የበጎ አድራጎት ክፍል አላማውን ለመፈፀም ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን
እነርሱም፡-
1. የውስጥ እርዳታ ክፍል
2. የውጭ እርዳታ ክፍል
3. ቤተ-መጻህፍት ክፍል ናቸው
ተግባር 
  1. 1.          በጎ አድራጎት ክፍል
1.1.  ሰ/ት/ቤቱን ንብረት መጠገን ሚገባቸውን በዕቅድ በመንደፍ በአመት ውስጥ የሚገኙበትን ፕሮግራም ማውጣትና ጥገናዎችን በተገቢው መንገድ መጠገን፣
1.2.  ጥገናንና የመሳሰሉትን ስራዎችን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን፣ ገንዘብና የመሳሰሉትን ለሚመለከተው ክፍል እንደየባህሪያቸው በደብዳቤ ወይም በወጭና በገቢ ፎርም በመሙላት ለተፈለገለት ጊዜ ማድረስ፣
1.3.  ማንኛውም የሞያ መገልገያ እቃዎች እንዲሞሉ ጥረት ማድረግና ያሉትንም በጥንቃቄ መያዝ፣
1.4.  የሞያ ክፍሉ በተለያዩ ዝግጅቶች /ሁኔታዎች በጉልበትም ሆነ በስጦታ መልክ አስተዋፆ የሚያደርጉ ሰዎችን ስማቸውን በመያዝ ለስራ ያላቸውን ብርታት ለጽ/ቤት በማሳወቅ ተገቢውን መንፈስ ብርታት የሚያገኙበትን መንገድ መፍጠር፣   
1.5.  በአባላት መሀከል የስራ ውድድርን በመፍጠር ሰ/ት/ቤቱ በክፍሉ የሚጎለብትበትን መንገድ መፍጠር
1.6.  በሴቶችና በወንዶች የእጅ ስራዎችን በመፍጠር የገቢ ማስገኛ ማዘጋጀት፣
1.7.  በሞያ ክፍል የተሠሩ ንብቶች /ዕቃዎች/ ስራቸው እንደተተናቀቀ ለንብረት ክፍል ህጋዊ በመሆን መንገድ መስረከብ፣
  1. 2.         የውስጥ እርዳታ
2.1.  ይህ ክፍል ማህበሩንና የቤተክርስቲያኒቱን አጠቃላይ ጽዳት የሚያደርግበት ፕሮግራም በማጣት ያከናውናል፣
2.2.  በዚህ ክፍል የሰ/ት/ቤቱን አልባሳት፣ አዳራሽና የመሳሰሉትን መደበኛ የሆነ ፕሮግራም በማውጣት ጽዳት እንዲደረግ ያደርጋል፣
2.3.  በሰ/ት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ አትክልቶችን መንከባከብ፣ መትከልና ግቢው ውበት እንዲኖረው ማድረግ፣
2.4.  በዚህ ክፍል አባላትን በቡድን በመከፋፈል የስራ ውድድርን መፍጠርና ስራቸውን በሚገባ በሚወጡ አባላት መንፈሳዊ ብርታት የሚያገኙበትን መንገድ መፍጠር፣

  1. 3.         የውጭ እርዳታ








ህፃናት ክፍል፣
የሕጻናት ክፍል አላማውን ለመፈፀም አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን
እነርሱም፡-
1. መዝሙር አስተባባሪ
2. ስነጽሁፍ አስተባባሪ
3. የአባላት ጉዳይ አስተባባሪ
4. መርሐ ግብር አስተባባሪ

ተግባር
1. ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ሆኖ የሚሰጡትን ትዕዛዛት ይፈፅማል፣
2. የህፃናት ክፍል በእድሜ ለሶስት ይከፈላሉ እነርሱም፡-
2.1.  ቂርቆስ፣
2.2.  እስጢፋኖስ፣
2.3.  አትናቴወስ፣
3. የህፃናትን ደረጃ ጠብቆ እንደ አቅማቸው እግዚአብሔርን ቃል /መጽሐፍ ቅዱስን/ ማስተማር፣
4. ህፃናት በመደበኛ ሰዓታቸው መጥተው ገባኤቸውን እንዲከታተሉ ማድረግ፣
5. ህፃናትን ከሁሉም በላይ ታሪክ ቢማሩ ለህይወታቸው ጥሩ ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው አስተዋፆ ስላለው ታሪክን በበለጠ ማስተማር፣
6. ለህፃናት የግብረ ገብነት ትምህርት በማስተማር ለቤተሰቦቻቸው እንዲታዘዙ የባህሪ ለውጥ እንዲያገኙ ማድረግ፣
7. የህፃናት ክፍል እድሜጣቸው ከ 15 ዓመት በላይ ሲሆን ወደ ወጣቶች ጉባኤ እንዲሳተፉ ለጽ/ቤቱ በደብዳቤ መጠየቅ፣
8. ህፃናትን ጎጅ ልማዶችን እንዲያስወግዱ ያስተምራል፣
9. የህፃናት ክፍሉ ከተለያዩ ሰ/ት/ቤቱ ህፃናት ክፍል ጋር እንደአስፈላጊነቱ የአንድነት ፕሮግራም ያዘጋጃል፣
  1. 10.          በጽ/ቤቱ የሚሰጡትን ተጨማሪ ጠግባራት ያከናውናል፡፡
  2. 11.          ህፃናት በመርሃ ግብራችን ላይ መዝሙር እና ስነ-ስሁፍ አጥንተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
  3. 12.          ከዚህ በተጨማሪ ራሱን የቻለ ውስጠ ደንብ ይኖረዋል
  4. 13.          በአጥቢያው ያሉትን ምዕመናን ልጆቻቸውን እንዲልኩ ቅስቀሳ ያደርጋል
አንቀፅ 9
በሰ/ት/ቤቱ የሚመሩ መርሀ ግብሮች
ሰ/ት/ቤቱ በስሩ የሚያስተዳድራቸው ሶስት የመርሃ ግብች ሲኖሩት
እነርሱም፡-
9.1. የሕፃት መርሃ ግብር
9.2. የወጣቶች መርሃ ግብርና
9.3. የጎልማሶች መርሃ ግብር ተብለው ይጠራሉ፣
9.4. ለሶስቱም መርሃ ግብሮች ሰ/ት/ቤቱ የሚለይበት በእድሜና በተለያዩ ጊዜያት እንደአስፈላጊነቱ መስፈርቶችን ያወጣል፡፡
መርሐ ግብር
1. ማስታወቂያ ክፍል
1. ማንኛው የሰ/ት/ቤቱ ማስታወቂያዎችን በበላይነት ይቆጣጠራል
2. ስ/ት ጊዜያቸውን እና ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲጣሩ ያደርጋል
3. ማህተም የሌላቸው እና መንፈሳዊ ያልሆኑ ማስታወቂያዎች በቤተክርስትያኑ አካባቢ እንዳይለጠፍ ይቆጣጠራል፡፡
2. አዳራሽ ዝግጅት እና መርሐ ግብር ቅንጅት
1. ለተለያዩ መርሐ ግብሮች አዳራሾችን ያፀዳል ያዘጋጃል
2. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመገናኘት የአዳራሹን አጠቃቀም ሰዓት ያወጣል፣ ተፈፃሚነታቸውን ይቆጣጠራል
3.  መርሐ ግብር መሪዎች ቁጥር
1. በሰ/ት/ቤቱ  ለሚካሄዱ ማንኛውም መርሀ ግብሮች መርሀ ግብር መሪዎች ይመድባል፣ ይቆጣጠራል፡፡
2. ለመርሐ ግብር መሪዎች ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመሆን ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
4. ወርሐዊ ጉባኤ እና ጽዋ መርሃ ግብር
1. በሰ/ት/ቤቱ የሚካሄዱ መርሐዊ ጉባኤዎች እና ጽዋ መርሃ ግብራትን ይቆጣጠራል፣ ጉባኤውን ያቀናጃል
2. በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከናወኑ ጽዋ መርሐ ግብር ይቆጣጠራል፡፡

አንቀጽ 10
የፅዋ ማህበራትን በተመለከተ
አንድ የፅዋ ማህበራት በቃላዋዲው መሠረት ሚተዳደር ሲሆን ሰ/ት/ቤቱ ስለ ጽዋ ማህበር ያሚያምነበትን መተዳደሪያ ደንብ መቀበል አለበት፡፡ ይህም ዝርዝር የአፈፃፀም ሂደት የሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት በሚሰጠው ህጋዊ ደብዳቤ መተዳደር አለበት፡፡
10.1.     የጽዋ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ

ከበፊቱ አጀዳ ያለው ይጻፍ
አንቀፅ 11
የአዳራሽ  አገልግሎትን በተመለከተ
የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት አዳራሽን ካለው የአገልግሎት እድሜና በውስጡ ያሉት የመገልገያ ዕቃዎች እድሜ ማጣት አንፃር ሰ/ት/ቤቱ ለአገልግሎት የሚከተሉትን መስፈርቶች ይጠይቃል፡-
1. በዕለ እሁድ የሰ/ት/ቤቱ መርሃ ግብር የሚስተናገድበት ስለሆነ ለማንኛውም አገልግሎት የማይውል መሆኑን ያሳውቃል፣
2. ለአዳራሹና በውስጡ ለምንገለገልባቸው ዕቃች መጠገኛ ጽ/ቤቱ በሚያወጣው የዝርዝር አፈፃፀም ኪራይ ይጠይቃል
3. አዳራሹ ሰ/ት/ቤቱ እንደመሆኑ መጠን ያለ ሰበካ ጉባኤ እና ያለ ሰ/ት/ቤቱ ፈቃድ ማንኛውም አካል /ማህበር ሊገለገል አይችልም፣




አንቀፅ 12
ማህበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ
ደስታ(መርቃት፣ክርስትና እና መንፈሳዊ ጋብቻ)
1. ሰ/ት/ቤቱ በዕለቱ ላለው መርሐ-ግብር ማስተናገጃ የሚሆን ብር ………………… ይጠይቃል፣
2. ሰርገኞች በሰ/ት/ቤቱ በመንፈሳዊ መዝሙር እንዲታጀቡ ሲጠይቁ ስራ አስፈፃሚ ተነጋግሮ  ያሳውቃል፣
3. አባል ላልሆኑ ሰርጋቸውን በመንፈሳዊ ጋብቻ ለሚፈጽሙ ሰርገኞች ስራ አስፈፃሚ ስለ ሰወቹ አጥርቶ እና ተነጋግሮ  ያሳውቃል (ተጨማሪ ክፍያ አይጠየቁም)፣
ሀዘን
1. አንድ የሰ/ት/ቤቱ አባል ሀዘን ቢደርስበት ሰ/ት/ቤቱ ሀዘንተኛውን የሚያፅናናበት መርሐ-ግብር አለው ይህን በተመለከተ የአፈፃፀም ሂደት ለአባላት በጉባዔ ያሳውቃል፣
ማሳሰቢያ
ስለ መተዳደሪያ ደንብ መሻሻል
  • ይህ ደንብ ከአባል አስከ ሥራ-አስፈጻሚ ድረስ የሚመለከት ሲሆን ለአባላቱ ከተገለፀበት እና ከተስማሙበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፣
  • ይህ መተዳደሪያ ደንብ በስራ ላይ ውሎ ከታየ በኋላ እንደአስፈላጊነቱ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሊሻሻል ይችላል፣
  • ይህ ደንብ የሚያገለግለው ለሚመለከታቸው አባላት በሙሉ ሲሆን ተፈጻሚነቱ  ለሰ/ት/ቤቱ አባላት ብቻ ነው፡፡
  • ይህ ደንብ በሰ/ት/ቤቱ ከሚገኙ ሌሎች ውስጠ ደንቦች ሁሉ የበላይ ነው፡፡

13 አስተያየቶች:

  1. እናመሰግናለን እ/ር ይስጥልን አሁንም መመሪያዎችና ደንቦች ቢለቀቁ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. እግዚአብሔር በሰራችን ሁሉ ይግባ አገልግሎታችንንም ይባርክልን

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. እግዚአብሔር አገልግሎታቹ ይባርክ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  4. እግዚአብሔር አግሎታችን ይባርክ ቃለ ህይወትን ያሰማልን። ከዚህ በተጨማሪ የማህበራት ውስጠ ደንብ በቸብራራ ሁናቴ ቢገለጽ?

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  5. እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክላችሁ።

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  6. Egziabher Yakbirilin.
    Lemin ye Limat kifl Dirsha Altezerezerem?

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  7. እግዚአብሔር አገልግሎቶችሁን ይባርክ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  8. እግዚያብሐር ይስጥልን ጥሩ መዋቅር ነው በዛው አይይዛቹህ የጽዋ ማህበራትን በዚህ መልክ ብታስቀምጡልን 🙏

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  9. እግዚአብሔር አምላክ ያሰባችሁትን ሊሳካላቸው

    ምላሽ ይስጡሰርዝ